የሲዳማ ህዝብ 7ኛውን አመት የ11/11 ግድያና 48ኛውን የ1970 ዓ/ም የቦሪቻና የወታራራሳ ህዝብዊ አምጽና የህዝብ እልቅት ሀምሌ 12ን ለመዘከር

ከሲዳማ ነጻነት ግንባርና ከሲዳማ ስብአዊ መብትች ካውንስል የተሰጠ መግለጫ:-

ሀምሌ 11/2018

ሐምሌ 11/2011 የዛሬ 7ኛውን አመት 11/11 በሚለው የሲዳማ ህዝብ በሰላም ህገመግስታዊ መብቱ (በ1995 ዓ/ም በተደነገገው አንቀጽ 39(1) ና47(2)} እንድከበርና  የክልል ጥያቄ ረፈረንደም ቀን እንድወስን ጥያቄ ለማቅረብ የወጣው ያልታጠቀውን ህዝብ  በግፍ በአብይ አህመድ መንግስት 163 ንጹሀን የተጨፈጨፉበት ቀን ሁልግዜ በህዝባችን ታሪክ ስያታወስ ይኖራል። በነዝህ ደም ላይ ተመስርቶ የክልልነት ጥይቄ መልስ ቢያገኝም  በአብይ አህመድ ሴራና ተንኮል  የክልሉ መንግስት እስከዛሬ “የከሸፈ መንግስት/አቅመቢስ መንግስት” (failed state) ሆኖ የገኛል፡፡

ከዝህ በተጨማሪ የሲዳማ ህዝብ 48ኛውን የቦርቻና የወታራራሳ ህዝብ በደርግ መንግስት ላይ ያከሄደውን አመጽ በተነሳ ብዙ ወገኖቻችን ላይ በደርግ ሰራዊት የተፈጸመውን ግድያና የተከፈለውን መስዋእት የህዝባችን ታሪክ ያስታውሰዋል። የቦርቻውን አመጽ የመሩት ቢትረ ገመዳ፤ የተራ ኮመ ና ህጊሶ ጋቸኖ ሲሆኑ የማልጋ አካባቢ የመራው አጋና ጃቢሳ ነበረ።እነዚህ ጅግኖች በንሳ አርቤጎና አሮረሳ እየትካሄድ በወቅቱ የነበረው የሲዳማ ነጻነት ንቅናቄ ጋር በመቀንጀት የተከሂደ ሲሆን አላማው የደርግን ሰራዊነት ከሲዳማ ጠራርጎ ለማስወጣት ነበረ.።፡በቦርቻኛ በወታራራሳና እንድሁም 6 አመት በፈጀው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ በተመራው ጦርነት በድምሩ  10000 በላይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ህይወታቸውን  ሰውተዋል።

የሲዳማ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ህዝቦች ግፍ ከተፈጸማባቸው አንዱ ሲሆን የዝህ ግድያ መንሴው ህዝባችን መብቴ ይክበር የራሰን ጉዳይ እራሴ ልፈጽም በማለት ለ135 አመታት የፈጀ ትግል አካህዶአል« ለህዝብ መብት ግድ የሌላቸው ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግስታት ይዘውለት የምቀርቡት ከዛሬም ጭምር ጥይትና ግድያ ብቻ ነው። ሌላው የኢትዮጵያ መንግስት መገለጫ  የሆነው የሎቄ ግድያ ነበረ.።፡የሲዳማ ታሪክ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል ቢባል አፈናና ግዲያ ብቻ ልባል ይገባዋል»

ያም ሆነ ይህ በአገርቷ ከነበሩትና ከአለፉት ስምንት አመታት ስንጻጸሩ  አብይ አህመድን ያህል በሲራና ተንኮል ሲዳማን ህዝብ ለማኮላሽት የሰራ መሪ የለም።አብይ ሀምሌ 11/211 ህዝባችን ብቻ አይደለም የገደለው የሲዳማ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን ነጥቆ ደካማና እውቀትቢሶችን በመሾም  ክልሉን የሌቦች መናኽሪያ አድርጎታል።የአቢይ አህመድ በተለይም በሲዳማ የ8 አመት ሥራ ውጤት ምንድነው? ቢባል አብይ  ሲዳማን የዝንጀሮ መፈንጫ ማድረግ ነበረ.። አድርጎታልም።

አሁን ደግሞ የ1995 ህገመንግስት በመናድና ፈደራላዊ መንግስት ለማፈራረስ  ሲዳማን ብቻ ሳይሆን የተረገጡ ብሄር ብሄረስቦችን ለመበቀል  እያሴረ ይገኛል። ስለሆነም ሲዳማና ሌሎች የተጨቆኑ ህዝቦች በጋራ በመነሳት አገርቷን የመሪነት ብቃት ከሌለው አብይ አህመድ እጅ በማውጣት 135 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን እንታደግ።

ድል ለሲዳማ ህዝብ!

ድል ለተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች!!


Discover more from Sidama Crisis Monitor

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a Reply

Discover more from Sidama Crisis Monitor

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Discover more from Sidama Crisis Monitor

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading