ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ/ም
ህዋሀት ከዘር ፍጅቱ ጦርነት በኋላ ትግራይ ቀድሞው ወደነበረችበት ህገመንግስታዊ ዲሞክራሲ በመመለስ ከጦርነቱ በፍት የተመረጠውን የትግራይ ም/ቤት ወደሥራው በመመለስና ደብረጽዮን ገ/ምካኤልን የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አድርጎ በመምረጥ የወሰደውን እርምጃ ተቀባይነት ያለው ብቻ ሳይሆን የትግራይን ሉአላዊነት በህገ መንግስቱ መሰረት ያረጋገጠ መብት መሆኑን የሲዳማ ነጻንት ግንባርና በአጽኖኦት ተመልክቶታል;፡ ይህም የፕርቶሪያው ስምምነት ከመፍረስ ጋር ያለው ሁኔታና ፋሽስታዊው የአብይ አስተዳደር የትግራይን ህዝብ ለሁለተኛ ዙር የዘር ማጥፋትከበባ ውስጥ በማስገባት በምሳለቅበት ወቅት በህዋሀት የተወሰደው እርምጃ ድንቅና ወቅታዊ መሆኑን በማመን ሙሉ ድጋፉችንን እንገልጻለን።
ድርጅቶቻችን ይህንን የአቢይ አህመድ ፋሽስታዊ የዘር ማጥፋት ከበባ ጦርነት ከ2020-2022 የተፈጸመ አሬመንያዊ ድርግት በተገኘው መረጃ መሰረት ከ1.2 ሚልዮን ተጋሩን ህይወት መቅጠፉ ልብ ሰባሪ የሆነ ስብአዊነት የጎደለው ተግባር ሲሆን ይህንን የፈጸሙ ዛሬም ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም እያደቡ ይገኛሉ።የትግራይ ህዝብና ተመሳሳይ ግፍ የተፈጸምባቸው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረስቦችና ህዝቦች ፍትህን ይሻሉ።
ዳግም ተጋሩ በከበባ ሥር ወድቆ ይገኛል። ይህም እርምጃ የትግራይ ህዝብ ዳግም በድምፅ የለሽ መሳሪያ ለመግደል ምግብና መድሀኒት እንድሁም መሰረታዊ የሆኑትን ቁሳቁሶች ትግራይ እንዳይገቡ በማድረግ ትግራይን ከፈደረሽኑ በመነጥል ፀረ-ህዝብ የሆነ ፋሽስታዊ ክበባ የሆነውን የመንግስት ፖሊስ አጥብቀን እንቃወማለን›። በተጋሩ ላይ እየተወሰደ ያለው የግፍና የጥላቻ ምንጩ በህወሀት መሪነት በብሄር ብሄረስቦች ሙሉ ድጋፍ የጸደቀውን የ1995 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ህገመንግስት ማጸደቁ አሮጌውን ሥርአት ናፋቂዎችና ተጠቃሚዎችን ጥላቻ ያረገዙ ሀይሎች በአብይ ብልጽግና አስተባባሪነት እንድዘምቱ ያደረገ ሲሆን ይህ በኢትዮጵያዊነት አዋዜ የተለከፈ ሀይል ተወፍታዊነት የሌለውን ማንነት በማላበስ ሀገመንግስቱን ለመሻር የተከደበት ርቀት መሆኑን ብሄር ብሄረሰቦች ልብ ልሉት ይገባል። ለዝህ ማስረጃ ካስፈለገ አብይ ወደ ሥልጣን በመጣ ጊዜ ለህዝብ በአደረገ ንግግር በግልጽ ያስቀመጠውና የገባው ቃል “ኢትዮጵያን ወደ ጥንቱ ዝናና ክብር” እመልሳለው ብሎ የገባን ቃል የአሁኑን ህገመንግስት አፈርሳለው ማለቱ መሆኑ ለተጋሩ ሆነ ለብሄር ብሄረስቦች ግልጽ ነበረ።የትግራይ ጦርነት የዝህ ድብቅ አላማ ጅማሮ ውጤት ነበረ።
ዛሬ በአረብ ኤመሬት ድጋፍ በኦሮምያ፡ በአማራና በደቡብ ኢትዮጵያና ሲዳማ ክልልን ጨምሮ የሚካሄደው አፈናና ግድያ የዝህ ህገመንግስት ማፍረስ ሂደት መሆኑን የሲዳማ አርነት ግንባር በሚገባ ተረድቶታል።ኢትዮጵያ ባለቤት የሌላት እየፈራረስች ያለች መሆኗን በአገርቷ እየተካሄደ ካለው ጦርነት በላይ ምንም ምሥክር አያስፈልገም.። አገርቷም የምትድነው ከውሸታም ዲይቆናት ፡ደብተራዎች፡ ካድረዎችና ነቢያት መላቀቅ ስትችልና፤የአሮጌው ሥርአት ናፍቅዎች የማይመለሰውን አሀዳዊነት እንመልስለን እያሉ ህዝባቸውን ከማጫረስ ተቆጥበው ሁሉን አቀፍ ወደሆነው ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርአት መመሥረት ቢያመሩ የተሻለ ይሆናል ብለን እናምናለን። ለዚህም እንታገላለን።
በመጨረሻም ሲዳማ አርነት ግንባር ለብሄር ብሄርስቦች የምያቀርበው ጥሪ ያለምንም ማወላወል የትግራይ ህዝብ የራሱን አስተዳደር መመስረቱ ሀገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን አምነን ተቀብለን ከጎናቸው እንድንቆምና ትግላቸውን እንድደግፍ ጥሪ እናቀርባለን።
ፍትህ ለኢትዮጵያ ብሄር ብሂረስቦች
ነጻነት ለትግራይና ለተቀሩት ብሂር ብሄረስቦች በኢትዮጵያ
የሲዳማ ብሐራዊ ነጻነት ግንባር

Leave a Reply