ታህሳስ 18/2018
በኢትዮጵያ የውስጥ እርስ በርስ ጦርነት የጀመረው የኤርትራ ፈደረሽንን የሀይለሥላሴ መንግስት ማፍረስ ተከትሎ ሲሆን ይህንን የአሃዳዊነትን የህዝብ መብት ጠላት የሆነውን ደካማ አስተሳሰብን ቀጣዩ የደርግ መንግስት ለማረም አልቻለም። በዛሬዋ ኢትዮጵያ በኮሎኔል አብይ አህመድ አሊ 1የምመራው የውሸት ብልጽግና መንግስት በተመሳሳይ ያለፈውን ስህተት ለማረም የወጣውን ፈደራላዊ ህገመንግስት ለማፍረስ የሄደበት ርቀት አገርቷን ለባሰ እልቀት ዳርጎአል። በአለፉት ሰባት አመታት ህዝቡ ያሳለፈው የልማትና የሰላም ጊዜ ሳይሆን የግድያና የሽብር ጊዜያት ናቸው። ለዝህ ዋናው ምክንያት በአገርቷ ያሉትን የፖለቲካ ቅራኔዎች በውይይትና በድርድር ከመፍታት ይልቅ ግጭቶችን በማባባስ አገርቷን የጦርነት ምድር ያደረገው የአብይ አህመድ አሊ አስተዳደር ነው። አብይ አህመድ አሊ ጦርነትን የስልጣን መቆናጠጫ መርህ አድርጎ የሚጠቀም ፣ ለሰው ልጅ ርህራሄ የጎደለው ፋሽስት መሆኑ በትግራይ ፣ በአማራ ፣ ኦሮሚያ ፣ በሲዳማ፡ በሱማሌና ፣ አፋር ክልሎች የተካሄዱት ግድያዎች በቂ ማስረጃዎች ናቸው።
በጦርነቱ ሳቢያ በአገርቷ ወጣቱ ሥራ አጥ ሆኖአል። ለወጣቱ ያለው እድል አብይ አህመድ አሊ በሚፈለፍላቸው ግጭቶች የሱን ሥልጣን ለመከላከል በውትድርና ተመልምለው የርስ በርስ ጦርነት እየተማገዱ መቀጠል ሲሆን ፤ እስካሁን በተካሄዱ የርስ በርስ ጦርነቶች የብዙዎች ወጣቶች የወደፍት ተስፋ ተቀጥፎአል። በየአካባቢው ህዝቦች እርስ በርሳቸው እንዲጋደሉ ተደርጓል። ህጻናት ያለወላጅና አሳዳጊ በማጣት በሜዳ ላይ ተበትነዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የህዝብ መሪዎች ተገድለዋል። ይህ ሁሉ ምስቅልቅል ለምን ቢባል:- ሆነ ተብሎ ሃገሪቷን የአረቦችና የቱርኮች መጠቀሚያ አድርጎ ለመሸንሸን የብልፅግና መንግስት በሚሰራ ሴራ መሆኑ የታወቀ ነው። እንደዚሁም የህዝብ ሃብትና ገንዘብ ተዘርፎአል። የዝህ ዝርፍያ ዋና ተዋናይ የውሸት ብልጽግና መንግስት ባልሥልጣናትና የፓርቲው አባላት ናቸው። አገርቷ የጉቦና የአፋኞች መናሀሪያ ሆናለች።
የሲዳማ ህዝብም የዚህ ሴራ ሰለባ ሆኖአል። የሲዳማ ወጣቶች የክልል ጥያቄ አራምዳችኋል በማለት ከ167 በላይ የሚሆኑት ያለፍርድ ተረሽነል. ከ100 በላይ የሚሆኑት ያለፍርድ ታስረው ይገኛሉ። አቶ ፍሰሀ ጋረደው በወቅቱ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር በተጠነሰሰው ሴራ የወላይታና የሲዳማ ህዝብ እንድጋጩ ተደርጓል። በሴራው ግድያዎች ሲፈጽሙ ፤ በዚህ ጉዳይ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የታሰሩ የወላይታ ወጣቶች ስፈቱ ፤ የሲዳማ ተዎላጆች ላይ ግን ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከ9-25 አመት ተፈርዶባቸው ወህኒ ወርደዋል። ይህ ጥላቻና መፈላለግ በሁለቱ ብሄርሰቦች መካከል እንድቀጥል ለማድረግ ሆን ተብሎ ታስቦ የተሰራ ሴራ ነው።
የሲዳማ ህዝብና ወጣቶች ሆይ!
ህዝባችን ለመብቱ ያደረገው ትግል በባንዳዎች (ቦሮጄዎች) ተጠልፎአል። ክልሉ የዘራፍዎች አውድማ ሆኖአል። ልጆችህ የባሌን በረሀ ተሻግረው ሱማሌ ሃገር ድረስ በመሄድ ሰልጥነውና ታጥቀው ያደረጉት ትግል ራስህን በራስ የማስተዳደር መብትህን ለማስከበር ነበረ። በልጆችህ ደምና አጥንት እንዲሁም የህይወት መስዋትነት ላይ ክህደት ተፍጽሞአል። በፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ተሿሚዎች ዛሬ ደግሞ የእነሱን ልጆች በአለም ዙሪያ ባሉ ምርጥ ዩንቨርስቲዎችና ባገር ውስጥ ምርጥ ት/ቤቶች እያስተማሩ ያንተን ልጆች ለወታደርነት እየመለመሉ በጦርነት እየማገዱ ይገኛሉ።
ለምሳሌ:- በሐዋሳ ዙሪያ ዶሬ ባፋኖ ቀበለ ከተመለመሉ ወጣቶች መካከል ብቻ በትንሹ ሰባቱ በአንድ ግዜ በቅርቡ በወሎ የብልፅግና 11ኛና 12ኛ ክፍለ ጦር ስደመሰስ በብዛት ያለቁት የሲዳማ ልጆች ናቸው። ለምንድነው የሲዳማ ልጆች የምሞቱት? ህዝብ እርስ በርሱ ለምን ይጋደላል? ይህ ጦርነት የሲዳማ ህዝብ ችግር አይደለም። ችግሩ የሴርኞችና ህገመንግስት አፍራሾች የነ አብይ አህመድ አሊ የብልጽግናዎች ችግር ነው።
ስለሆነም ልጆችህን ከሲዳማ ብሄራው ክልል ውጪ ፈፅሞ መላክ የለብህም። ይህ እውን እንድሆን ተመሳሳይ አላማ ካላቸው ፖለቲካ ሀይሎች ጎን በመሰለፍ በሰላማዊ ትግል ይህንን ፋሽስት መንግስት ለማስወገድ በንቃት በመሳተፍ ልጆችህን እንድትታድግ ጥሪ እናቀርባለን።
ጦርነት ይቁም!
ድል ለህዝባችንና ለመላው ኢትዮጵያ ህዝቦች!!
ታህሳስ 18/2018

Leave a comment