ለኢትዮጵያ ፈደራላዊ አቃቤ ህግ ፅ/ቤት

ፋክስ 25111551-77-75

ስልክ ቁጥር +251115515099

ፖስታ ሳጥን ቁጥር (P.O BOX) 1370

 አዲስ አበባ

ጉዳዩ በግፍ ተፈርዶባቸው ያሉና እንድሁም ያለፍርድ ታሰረው ስለምገኙ የሲዳማ ተወላጆች በተመለከተ

የታሰሩበት ቦታ ሀዋሳ ወህኒ ቤት ሲሆን ፤ ጊዜው 2016 አ/ም ነበረ። ጠቅላይ ምንስተር አብይ አህመድ በወቅቱ ጠቅላይ ምንስተር የነበረውን ሀይለማሪያም ደሳለኝን  በኦሮሞ ወጣቶች /ቀሮ ንቅናቄ/ መስዋእትነት ከሥልጣን አስወገዶ ሥልጣን ላይ ወጥቶ የነበረበትና የግንቦት 7 ሴራ ተንሰራፍቶ ፀረ-ኦሮሞ ግድያዎች በናዝረት ፡ አዲስ አባባና ፤ ፀረ-ሲዳማ የሆነ ሴራ በሀዋሳ  ወያኔ አደረገ  በሚል ፕሮፓጋንዳ ሽፋን በከንቱ የንፁሀን ደም የምፈስበት ወቅት ነበረ። በሌላ ጎን በሲዳማ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ይከበርልኝ እያለ ክልል የመሆን ጥያቄ አንግቦ የተነሳበት ህጋዊ ጥያቄ በክልሉና በፈደረሸን ም/ቤት ተወስኖ ምርጫ ቦርድ ላይ የተቀመጠችው የፍትህ ቀበኛ የሆነችው የግንቦት 7 አባል ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ ከረፈረንደሙ በፍት ካለ ሀገ-መንግስታዊ መብቷ ሲዳማና ደቡብ ክልል ንብረት ካልተከፈላችሁ በማለት ረፈረንደም ከማካሄድ ፋንታ ያልተፃፈ ህግ የምታነብበት ወቅት ነበረ። ይህንን የህዝቡን ህገ-መንግስታዊውን ጥያቄ የፀጥታና የአገር ደህንነት ጥያቄ ለማድረግና ለማክሸፍ ሴራ ይጠነሰሳል። ወያኔ አደረገ ለማሰኘት በሀዋሳ ከተማ በምገኘው መምህራን ኮሌጅ ተማሪ የሆነውን የሲዳማ ብሄር አባል ከላይብራሪ ስወጣ ያለ ምንም ሀጥአቱ የወላይታ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆነ ወታደር በጥይት ደብድቦ እንድገለው ይደረጋል። ይህንን የመራውና አስፈፀመ የሚባለው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር  የወላይታ ብሄር ተወላጅ የሆነው አቶ ፍሰሀ ጋረደው ነበረ ይባላል። ገዳይ ወታደር አልታሰረም ፤ እንድያውም አልተጠየቀም። ይህም በሲዳማ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ቁጣን ቀስቅሶ ፤  ለፍትህ ብሎ  የተነሳው ህዝብ አሁንም ዳግም ተጨፈጨፈ።  በወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የነበሩ የሲዳማ ብሄር  ሁለት ልጃገረዶች ከሚኖሩበት ዶርሚቴሪ ፎቅ ላይ ተወርውረው በወላይታ ተወላጆች ተገደሉ። ከዚህም የተነሳ የሲዳማ ተወላጆች ራስን የመከላከል (self defense) እርምጃ ይወስዳሉ። በወቅቱ ተደራጅቶና ታጥቆ የነበሩ የወላይታ ተወላጆች ብዙ ሲዳማዎችን ገደሉ። የነ አቶ ፍሰሃ ጋረደው ቡድን ሴራ ተሳካ። ከሁለቱም ወገን ሰዎች ታሰሩ። ከዝህ በኋላ ሁለተኛው ሴራ ዳግመኛ ተጠነሰሰ። ሆዳም የሆኑ እውነትን የተፀየፉ የሁለቱም ብሄር ሽማግሌዎች ነን ባዮችና የሀይማኖት መሪዎች ተብዬዎች እምነትን ቀርጥፈው የበሉ በማስታረቅ ስም ገብተው ሴራ ጠንሳሽ ወገን የሆኑት የወላይታ ተወላጆች እንድፈቱ ስያደረጉ ፤ የሲዳማ ተወላጆች ግን ከአምስት እስከ ሃያአምስት (5-25) አመት ተፈረደባቸው። አስታራቂዎች ተብለው የተመለመሉ ሰዎች እነ ፓስተር ጌቱ አያሌውን ጨምሮ በሀዋሳና በወላይታ ሶዶ ድግስ ተደገሰላቸው። በወቅቱ ሲዳማ በወታደራዊ ኮማንድ ሥር ወደቀች ። አቶ ፍስሀ ጋረደውም ለሰራው ሥራ ውለታ ከሀዋሳ ዞር ተደርጎ በአዲስ አበባ ከተማ የህግና ሥነሥርአት ክፍል ሀላፊ አድርገው እነ አብይ አህመድ፣ ሙፍሪያት ከማል፣ እና አዳነች አቤቤ ሾሙት። አቶ ፍሰሀ ጋረደው ዛሬ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ነው። ወያኔን ለመክሰስ በተደረገው ሴራ በማያውቁት ጉዳይ የሁለቱም ብሄርስብ አባላት ግን ከፍተኛ ዋጋ ከፈሉ። የዚህ ሁሉ ሴራ ጠንሳሽና መሪዎች በሙፍሪያት ከማልና ፣ ብርሀኑ ነጋ የምመራው ነፍሰገዳይ ቡድን ህዝባችንን ፍትህ አሳጥቶ ዛሬም እየጋለበ ይገኛል። በየቢሮው ለነሱ ያደሩ ሆዳሞችን በመሾም ህዝቡን መብት አልባ አድርገውታል። ብርሀኑ ነጋና ሙፍሪያት ከማል ለአቢይ አህመድ በግል ታማኝ ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ለሲዳማ ህዝብ ግን አይደሉም ፤ ለወደፊትም ሊሆኑ አይችሉም። አለመሆናቸውን ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። ከዚህ ጋርም ተያያዥነት ያለው አስራአንድ አስራአንድ (11:11) ተብሎ በሚታወቀው የክልል ጥያቄ ላይ በአተኮረ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ምክኒያት ከመቶ (100) በላይ የሲዳማ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች ዛሬም ድረስ ያለፍርድ ታስረው ይገኛሉ። የክልሉ ጥያቄ መልስ ከአገኘ ዛሬ መንግስትም ራሱን በአወቀበት ዘመን እነዚህ ወጣቶች ለምን ይታሰራሉ? ጉልበት ያለው ምን ታመጣለህ ካለ ፍትሀዊነት አይደለም።

ይህንን ጉዳይ መፍትሄ ያገኛል ብሎ የሲዳማ ስብአዊ መብት ተሟጓቾች በጥያቄ እስከዛሬ ክትትል ስያደርግ ቆይቶአል።

1ኛ) ይህንን ጉዳይ ለተከበረው መሥሪያ ቤት የምናቀርበው የተጓደለ ፍትህ ቂምን ይወልዳል ፤ የህዝቡን ማህበራዊ ትስስር (social fabric) ከማናጋት ባሻገር የተዳፈነ እሳት ሆኖ እንደምቆይ መረሳት የለበትም። በተለይ ህዝብ ከህዝብ ያደረገው ግጭት በሴራና ተንኮል አይፈታም። ሲዳማ የምናገርለት ለመንግስት ቅርበት ያለ ሰውም የለውም። በባህላዊ መንገድ ፍታነው ለማሰኘት የተከደበት መንገድ አንዱን ገድሎ ሌላውን ያዳነ አይነት በመሆኑ ፍትሀዊ ነው አያሰኝም። ፈረንጆች እንደሚሉት travesty of justice ይሆናል። የሲዳማ ስብአዊ መብት ተሟጓቾች ድምፅ ላጣው የሲዳማ ህዝብ ድምፅ መሆኑ በወንጀሉ ተሳታፍዎችንና የክልሉን አመራር ልያናድድና ልያበሳጭ ይችላል። ምክንያቱም የሙፍሪያት ከማል ተመራጮች እንጂ ሲዳማን ስለማይወክሉ ነው።

2ኛ) ያ ወቅት አልፎአልና ወገኖቻችን ፍትህ አግኝተው ማስተካከያ ተደርገው አንድፈቱ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ነው። ዝምታ ወርቅ ነው። ፍርሀት አይደለም። ህዝባችን ህግ አክባሪ ነው። አሁንም በአፋኞች ታፍነው ዜጎቻችን በግፍ መቀጠል የለባቸውም።

3ኛ) በሰለጠነው አለም ወጣቶች ካጠፉ ማረሚያ ትምህርት ይስጣቸዋል እንጅ መንግስት ለጥፋቱ ዜጎችን አይበቀልም። በውቅቱ ወንጀል አስፈፃሚዎች በህዝብ መካከል እንድገቡ ተደረጎ በዛሬዎቹ ሹመኞች የተሰራ ወንጀል በመሆኑ ለታሳሪዎች ፍትህን አዛብቶታል።

4ኛ) የፍትህ ማስተካከይ (legal remedy) በአግባቡ በጠበቃና በመከላከያ ያልተደገፈ በአጠቃላይ የደቦ ፍርድ (mob justice) በመሆኑ መንግስት ለሰራው ጥፋት ግልፀኝነት (transparency) ባለው መንገድ ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ ያለፍትህ ታስረው የሚገኙ የሲዳማ ተወላጆች በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው ብለን አጥብቀን እንጠይቃለን።

5ኛ) የወላይታ ተወላጆች የትውልድ ቦታቸውን ለቀው ሲዳማ የመጡት ኑሮው ይሻለናል ብለው ሲሆን ፤ በሀይለማሪያም ደሳለኝና ፍስሀ ጋረደው ተመክተው የተቀበላቸውን ለዘመናት አብረው የኖሩትን ህብረተስብ አክብረው መኖር እንጂ ግፍ መፈፀም ከነውርም በላይ ነውር ነው። ለማነው መሳሪያ የሚሆኑት? ለምን? ማንም መጥቶ ሲዳማ ውስጥ ስኖር እንደ ሲዳማ ነው መኖር ያለበት። ፈርንጆች እንድህ ይላሉ “when you live with others live like an envelope”። ምግባረ ብልሹ ከመሆን ሌላ ምን ይባላል።

6ኛ) ፍትህ በቀል አይደለም ፤ የገደለው እያለ የቆሰለውንና የሞተውን ወገን በደለኛ ማድረግ ፍትህ በላነት ወይም ፍርደ ገምድልነት (injustice) እንጂ ሌላ ልባል አይቻልም። በጣም አሳዛኙ ነገር ደግሞ ዳኞች ተብለው የተመረጡት የሲዳማ ተወላጆች ሲሆን ፤ ይህም የተደረገው በራሳቸው ሰዎች ላይ ፈረዱ ስለዚህ ፍርዱም ፍታዊ ነው ለማሰኘት የተከደበት ርቀት ነበረ። ወይንስ ለሥልጣንና ገንዘብ ፤ ካልሆነም እውቀት አንሶአቸው ይሆን አይታወቅም እንደዝያ አይነት ፍርድ የሰጡት። ይህ ወደፊት የተረጋጋ አገር ሲኖረን በሚገባ መጠናት (investigate) ያለበት ጉዳይ ነው። በፋሺስት ናዚ ግድያ ወቅት አይሁዶችን ዕየጦቆሙ ያስጨረሱት አይሁዶች እንደነበሩ የተጠናው ጥናት በቂ ምስክር ሆኖ እያገለገለ ይግኛል። ማንም ማንንም የመግደል መብት የለውም። በሲዳማ ሥልጣን አለን ባዮች ህዝባችንን ያለርህራሄ ገድለዋል። ፍትህን አሳጥተዋል። ግዜና ትግስት (time and patience) ይስጠን እንጂ ሁሉም ለሰራው ወንጀል ተመጣጣኝ ፍትህ ከማግኘት አያመልጥም።

የተከበሩ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆይ፣

የመተው ሞቶአል፡ የታሰረው ታስሮ ተሰቃይቶአል፤ ፍትህ ቢዘገይም ይደርሳል። በዚያች አገር ካለው ውዥንብር ነፅተው  ታሪክ እንድሰሩ በአክብሮት እንጠይቃለን። የእርሶ መመሪያ ህግና ህገመንግስት ብቻ በመሆኑ በዘመንዎ ለህዝባችን ሙሴ እንድሆኑልንና ፍትህን እንድያስፍኑልን የታሪክ አደራ እንላለን።

ፍትህና ዲሞክራሲ ለህዝባችን።

የሲዳማ ስብአዊ መብት ተሟጓቾች ኮሚቴ

ግልባጭ

Horn of Africa human right committee

USA mission in Ethiopia

European Human right

Norwegian mission Ethiopia

European representative Addis Ababa


Discover more from Sidama Crisis Monitor

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a comment

Discover more from Sidama Crisis Monitor

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading